የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ

የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዘጠነኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ንአከበረ

flag

ጥቅምት 07/2009 ዓ.ም

‹‹ሰንደቅ ዓላማችን የሉአላዊነት መገለጫ፤ ብዝሀነት ላይ ለተመሰረተው አንድነታችን አርማነው›› በሚል መሪ ቃል ብሄራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተቋሙ ግቢ በተከበረበት ወቅት የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሸብር ተክሌ ‹የብሄር ብሄረሰቦች የጋራ ሀብት፣ የሀገራችን ኩራት፣የማንነታችን መገለጫና የሀገራዊ ሜጋፕሮጀክቶቻችን ልዩ ምልክት የሆነው ሰንደቅ ዓላማችን ክብር ለማስጠበቅ ሁላችንም የሀገራችንን ሰላም በመጠበቅና በተሰማራንበት የስራ መስክ ጠንክረን በመስራት ሃላፈነታችን ልንወጣ ይገባል› በማለት ተናግረዋል፡፡

በበዓል አከባበሩ የተቋሙ የበላይ ሃላፊዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ መምህራንና ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን በበዓሉ መጨረሻም በህዝብና ዓለም አቀፍግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  ዶ/ር ክብረወርቅ ለማ አማካኝነት የቃለ መሀላ ስነ-ስርዓት ተደርጎ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ከቀኑ 5፡30 ሰንደቅ ዓላማውን በመስቀል የበዓሉ ፍፃሜ ሆኗል፡፡

Leave a Reply