የCTTI የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ተመሰረተ

የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ተመሰረተ፡፡

 

ጥር 18/2009 ዓ.ም በገነት ሆቴል በተደረገው የህብረቱ ምስረታ በክብር እንግድነት የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስተር ሚንስትር ዶክተር ሂሩት ወልደ ማርያም የሀገራችንን የባህልና የቱሪዝም ሀብት በማስተዋወቅ፣ ለዘርፉ እድገት የበኩላችሁን ለማበርከት ብሎም የዘርፉን ያልተነካ ሀብት ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት አስተዋፅኦ ያደርግ ዘንድ የአንጋፋው ተቋም የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት መመስረት ሚናው የጎላ በመሆኑ ተጠናከሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሸብር ተክሌ በበኩላቸው የህብረቱ መመስረት በተቋሙ ተመርቀው ለሀገሪቱ የሆቴልና የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ እያደረጉ ያሉ የቀድሞ ተማሪወችን በማሰባሰብ ከዚህም በላይ ለዘርፉ እድገት አስተዋፅኦ ያበረክቱ ዘንድ በማሰብ መሆኑን ጠቁመው ለዚህም ተቋሙ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ እና ለግቡ ስኬት አባላቱና አመራሩ በቅንጅት መስራት እንደለባቸው አሳስበዋል፡፡

 

በመጨረሻም የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት ሰባት አባለት ያሉት ኮሚቴ በመምረጥ ሰብሰባውን አጠናቋል፡፡

 

 

Leave a Reply